Update Quote

Update Well Said Quotes .

Author Title
Category Quote inamharic
Loading...

Glossary

ሜድቴሽን (Meditation)

ቁጭ ተብሎ ትንፋሽን ልብ ማለት ወይም ረጋ ብሎ በመራመድ አካልና አእምሮን የመገንዘብ ልምምድ

ማስተዋል (Mindfulness)

ነገሮችንን ሁኔታዎችን ረጋ ባለ ቀልብ ማየት

ቡዲሂዝም (Budhhism)

ሳዳርታ ጎታማ የተባለ ህንዳዊ ስለአእምሮአቸን እውነታ ያስተማረው ትምህርት ስም።

ዳሃማ (Dhamma)

ቡዳህ ያስተማረው ትምህርት

አራቱ እውነቶች (4 Noble Truths)

የቡድሃ አስተምህሮ ዋና አካል የሆነ፣ ስቃይና እና እርካታ የማጣት እንዳለ የሚያመለክት ከዛ መንስኤውንና ማቆም እንደምንችልና እንዴት እንደምናቆመው የሚያሳየን ትምህርት ነው።

ፍቅራዊ ደግነት (Loving-Kindness)

ለሁሉም ፍጥረታት ከራስ ጀምሮ ከሥቃይ እና ከስቃይ ምክንያቶቹ ነፃ እንዲሆኑ የመሻት ጥልቅ ፍላጎት እና ምኞት።

ሱታ (Sutta)

በቡድሃ ያስተማረውን ትምህርት የያዘ መመሪያ

የነቃ (Awaken )

አእምሮአዊ ስቃይ በሚቆምበት ግዜ የምንጠቀመው ቃል። ለቡዳ ይህ ቃል የተሰጠው አእምሮአዊ ስቃዩን ማቆም ስለቻለ ነው።

አጃን (Ajahn)

የታይላንድ ቃል፣ ለአስተማሪ ወይም ለአማካሪ።

ቢኩ (Bhikkhu)

የቡድሂስት መነኩሴ

ዘን (Zen)

በቻይንኛ ቻን ተብሎ የሚጠራ ቻይና ውስጥ የዳበረ የቡዲስት የሜድቴሽን አይነት ከአምስተኛው እስከ ሰባተኛው ክፍለ ዘመን ደግሞ ወደ ጃፓን እና ኮሪያ ተሰራጭቶ ዘን ተብሎ የሚጠራ ልምምድ።

ጊዜያዊነት (Impermanent)

ሁሉም ነገር ጊዜያዊና የሚለዋወጥ መሆኑን፣ ከሥጋዊ ነገሮች እስከ ሀሳቦች እና ስሜቶች ድረስ፣ እነዚህን የሚገልጽ የቡዲዝም ትምህርት።

መጣበቅ (Attachment)

የሚያልፉ ሁኔታዎችና ነገሮችን የደስታና የምኞቶች መንስኤ አደርጎ የሚቆጥር የተታለለ የአእምሮ ሁኔታ።

ማራ (Mára )

በቡድሂዝም ውስጥ የሚታወቀው ሰዎችን በመፈታተን ነው፣ ሱታዎች ላይ የተወከለው እንደ ክፉ አስተሳሰብ ያለው ሃይል ሰዎችን ከነጻነት መንገድ ለማራቅ የሚሞክር ሃይል ነው። ተሯሚዎች ማራን የክፉ ኃይሎች ጌታ፣ እንደ አእምሮ ርኩሰት እና እንደ ሞት ያስረዱታል።

ባዶነት፡ (Emptiness )

ነገሮችና ሁኔታዎች ራሳቸውን ችለው እንደማይነሱ፣ ነገር ግን እርስ በርስ የተያያዙ እና ከተፈጥሯዊ ወይም የተለየ የራስ ህልውና ባዶ መሆናቸውን የሚያመለክት ቃል ነው።

Gautama Buddha

— Founder of Buddhism

ጥፋቶች በጥልቀት ስለማየት

If a person has many offenses and does not repent of them, but cuts off all thought of repentance, the offenses will engulf him, just as water returning to the sea will gradually become deeper and wider. If a person has offenses and, realizing they are wrong, reforms and does good, the offenses will dissolve by themselves, just as a sick person who begins to perspire will gradually be cured."

In Amharic

አንድ ሰው ብዙ ጥፋቶች ካሉበት እና ተጸትቶ ጥፋቶቹን ካላቋረጠ፣ ወደ ባህር እንደሚመለስ ውሃ ቀስ በቀስ እየጠነከረ እና እየሰፋ ሄዶ በጥፋቶቹ ይዋጣል። አንድ ሰው ጥፋት ቢሰራም ስሕተቱን አውቆ ካስተካከለና መልካም መልካሙን ካደረገ ጥፋቱ በራሱ ግዜ ይጠፋል፤ ላብ የጀመረው ሕመምተኛ ቀስ በቀስ እንደሚድነው።

About

በተለምዶ ቡድሃ ተብሎ የሚጠራው ሲድሃርታ ጋውታማ በደቡብ እስያ በ6ኛው ወይም በ5ኛው መቶ ክፍለ ዘመን የኖረ እና ቡድሂዝምን የመሰረተ የባሕታዊ እና የሃይማኖት አስተማሪ ነበር።

Copyright © 2026
Made with ❤️ By Joe