Update Quote

Update Well Said Quotes .

Author Title
Category Quote inamharic
Loading...

Glossary

ሜድቴሽን (Meditation)

ቁጭ ተብሎ ትንፋሽን ልብ ማለት ወይም ረጋ ብሎ በመራመድ አካልና አእምሮን የመገንዘብ ልምምድ

ማስተዋል (Mindfulness)

ነገሮችንን ሁኔታዎችን ረጋ ባለ ቀልብ ማየት

ቡዲሂዝም (Budhhism)

ሳዳርታ ጎታማ የተባለ ህንዳዊ ስለአእምሮአቸን እውነታ ያስተማረው ትምህርት ስም።

ዳሃማ (Dhamma)

ቡዳህ ያስተማረው ትምህርት

አራቱ እውነቶች (4 Noble Truths)

የቡድሃ አስተምህሮ ዋና አካል የሆነ፣ ስቃይና እና እርካታ የማጣት እንዳለ የሚያመለክት ከዛ መንስኤውንና ማቆም እንደምንችልና እንዴት እንደምናቆመው የሚያሳየን ትምህርት ነው።

ፍቅራዊ ደግነት (Loving-Kindness)

ለሁሉም ፍጥረታት ከራስ ጀምሮ ከሥቃይ እና ከስቃይ ምክንያቶቹ ነፃ እንዲሆኑ የመሻት ጥልቅ ፍላጎት እና ምኞት።

ሱታ (Sutta)

በቡድሃ ያስተማረውን ትምህርት የያዘ መመሪያ

የነቃ (Awaken )

አእምሮአዊ ስቃይ በሚቆምበት ግዜ የምንጠቀመው ቃል። ለቡዳ ይህ ቃል የተሰጠው አእምሮአዊ ስቃዩን ማቆም ስለቻለ ነው።

አጃን (Ajahn)

የታይላንድ ቃል፣ ለአስተማሪ ወይም ለአማካሪ።

ቢኩ (Bhikkhu)

የቡድሂስት መነኩሴ

ዘን (Zen)

በቻይንኛ ቻን ተብሎ የሚጠራ ቻይና ውስጥ የዳበረ የቡዲስት የሜድቴሽን አይነት ከአምስተኛው እስከ ሰባተኛው ክፍለ ዘመን ደግሞ ወደ ጃፓን እና ኮሪያ ተሰራጭቶ ዘን ተብሎ የሚጠራ ልምምድ።

ጊዜያዊነት (Impermanent)

ሁሉም ነገር ጊዜያዊና የሚለዋወጥ መሆኑን፣ ከሥጋዊ ነገሮች እስከ ሀሳቦች እና ስሜቶች ድረስ፣ እነዚህን የሚገልጽ የቡዲዝም ትምህርት።

መጣበቅ (Attachment)

የሚያልፉ ሁኔታዎችና ነገሮችን የደስታና የምኞቶች መንስኤ አደርጎ የሚቆጥር የተታለለ የአእምሮ ሁኔታ።

ማራ (Mára )

በቡድሂዝም ውስጥ የሚታወቀው ሰዎችን በመፈታተን ነው፣ ሱታዎች ላይ የተወከለው እንደ ክፉ አስተሳሰብ ያለው ሃይል ሰዎችን ከነጻነት መንገድ ለማራቅ የሚሞክር ሃይል ነው። ተሯሚዎች ማራን የክፉ ኃይሎች ጌታ፣ እንደ አእምሮ ርኩሰት እና እንደ ሞት ያስረዱታል።

ባዶነት፡ (Emptiness )

ነገሮችና ሁኔታዎች ራሳቸውን ችለው እንደማይነሱ፣ ነገር ግን እርስ በርስ የተያያዙ እና ከተፈጥሯዊ ወይም የተለየ የራስ ህልውና ባዶ መሆናቸውን የሚያመለክት ቃል ነው።

Sayadaw U Tejaniya

— Buddhist Monk

ባላቸው ሃይል ስለሜድቴሽን

Many meditators think that being aware means focusing on an object with a great deal of energy. In fact, exertion like this causes tension because it’s the result of trying hard to create a positive or happy state of mind, which actually is the unwholesome root of greed at work. Instead, as you maintain continuous awareness of whatever is happening, strike a balance between being relaxed and being interested.

In Amharic

ብዙዎች ሜድቴት ማድረግ ማለት ባላቸው ሃይል ትንፋሽ ላይ ማተኮር ነው ብለው ያስባሉ። እንደ እውነቱ ከሆነ፣ እንዲህ ዓይነቱ ጥረት ውጥረትን ያስከትላል ምክንያቱም ደስተኛ የአእምሮ ሁኔታ ለመፍጠር እራሳችንን እያስጨነቅነው ስለሆነ ፣ ይህም ጤናማ ያልሆነውን የስግብግብነት ሥር ነው። ይልቁንስ ምን እየተፈጠረ እንዳለ ያለማቋረጥ በመገንዘብ፣ ዘና በማለትና በፍላጎት መካከል ሚዛኑን እንጠብቅ።

About

ሳያዳው ኡን ትጅኒ ቻይናዊ የቴራቫዲን ቡዲስት መነኩሴ እና በያንጎን፣ ሚዬንማር የሚገኘው የ Shwe Oo Min Dhamma Sukha Forest የሜድቴሽን ማእከል መምህር ሲሆን ትምህርቶቹ አለም አቀፍ ተመልካቾችን የሚስብ ነው።

Copyright © 2026
Made with ❤️ By Joe