Update Quote

Update Well Said Quotes .

Author Title
Category Quote inamharic
Loading...

Glossary

ሜድቴሽን (Meditation)

ቁጭ ተብሎ ትንፋሽን ልብ ማለት ወይም ረጋ ብሎ በመራመድ አካልና አእምሮን የመገንዘብ ልምምድ

ማስተዋል (Mindfulness)

ነገሮችንን ሁኔታዎችን ረጋ ባለ ቀልብ ማየት

ቡዲሂዝም (Budhhism)

ሳዳርታ ጎታማ የተባለ ህንዳዊ ስለአእምሮአቸን እውነታ ያስተማረው ትምህርት ስም።

ዳሃማ (Dhamma)

ቡዳህ ያስተማረው ትምህርት

አራቱ እውነቶች (4 Noble Truths)

የቡድሃ አስተምህሮ ዋና አካል የሆነ፣ ስቃይና እና እርካታ የማጣት እንዳለ የሚያመለክት ከዛ መንስኤውንና ማቆም እንደምንችልና እንዴት እንደምናቆመው የሚያሳየን ትምህርት ነው።

ፍቅራዊ ደግነት (Loving-Kindness)

ለሁሉም ፍጥረታት ከራስ ጀምሮ ከሥቃይ እና ከስቃይ ምክንያቶቹ ነፃ እንዲሆኑ የመሻት ጥልቅ ፍላጎት እና ምኞት።

ሱታ (Sutta)

በቡድሃ ያስተማረውን ትምህርት የያዘ መመሪያ

የነቃ (Awaken )

አእምሮአዊ ስቃይ በሚቆምበት ግዜ የምንጠቀመው ቃል። ለቡዳ ይህ ቃል የተሰጠው አእምሮአዊ ስቃዩን ማቆም ስለቻለ ነው።

አጃን (Ajahn)

የታይላንድ ቃል፣ ለአስተማሪ ወይም ለአማካሪ።

ቢኩ (Bhikkhu)

የቡድሂስት መነኩሴ

ዘን (Zen)

በቻይንኛ ቻን ተብሎ የሚጠራ ቻይና ውስጥ የዳበረ የቡዲስት የሜድቴሽን አይነት ከአምስተኛው እስከ ሰባተኛው ክፍለ ዘመን ደግሞ ወደ ጃፓን እና ኮሪያ ተሰራጭቶ ዘን ተብሎ የሚጠራ ልምምድ።

ጊዜያዊነት (Impermanent)

ሁሉም ነገር ጊዜያዊና የሚለዋወጥ መሆኑን፣ ከሥጋዊ ነገሮች እስከ ሀሳቦች እና ስሜቶች ድረስ፣ እነዚህን የሚገልጽ የቡዲዝም ትምህርት።

መጣበቅ (Attachment)

የሚያልፉ ሁኔታዎችና ነገሮችን የደስታና የምኞቶች መንስኤ አደርጎ የሚቆጥር የተታለለ የአእምሮ ሁኔታ።

ማራ (Mára )

በቡድሂዝም ውስጥ የሚታወቀው ሰዎችን በመፈታተን ነው፣ ሱታዎች ላይ የተወከለው እንደ ክፉ አስተሳሰብ ያለው ሃይል ሰዎችን ከነጻነት መንገድ ለማራቅ የሚሞክር ሃይል ነው። ተሯሚዎች ማራን የክፉ ኃይሎች ጌታ፣ እንደ አእምሮ ርኩሰት እና እንደ ሞት ያስረዱታል።

ባዶነት፡ (Emptiness )

ነገሮችና ሁኔታዎች ራሳቸውን ችለው እንደማይነሱ፣ ነገር ግን እርስ በርስ የተያያዙ እና ከተፈጥሯዊ ወይም የተለየ የራስ ህልውና ባዶ መሆናቸውን የሚያመለክት ቃል ነው።

Sayadaw U Tejaniya

— Buddhist Monk

ሀሳቦች ተፈጥሮ ናቸው ሰለጥበብ

Thoughts are nature. Thoughts are a process of mind. We should recognize thoughts, acknowledge them. Thoughts are not a problem. It’s important not to struggle with your thoughts. Our thoughts tell a story. This story is just a concept. It is not what or who we are. Thoughts may be about the past or the future. But that’s not so important. The mind is thinking. If you know that, that is good enough.

In Amharic

ሀሳቦች ተፈጥሮ ናቸው። ሀሳቦች የአእምሮ ሂደት ናቸው። ሃሳቦችን ልንገነዘብና እውቅና ልንሰጣቸው ይገባል። ሀሳቦች ችግር አይደሉም። ከሀሳቦችዎ ጋር አለመታገል አስፈላጊ ነው። ሀሳቦቻችን ታሪክን ይናገራሉ። ይህ ታሪክ ጽንሰ-ሐሳብ ብቻ ነው። ምን ወይም ማን እንደሆንን አይደለም የሚናገሩት። ሀሳቦች ያለፈው ወይም ሰለወደፊቱ ሊሆኑ ይችላሉ። ግን ያንን መስማት በጣም አስፈላጊ አይደለም። አእምሮ እያሰበ ነው። ይህን ካወቅን በቂ ነው።

About

ሳያዳው ኡን ትጅኒ ቻይናዊ የቴራቫዲን ቡዲስት መነኩሴ እና በያንጎን፣ ሚዬንማር የሚገኘው የ Shwe Oo Min Dhamma Sukha Forest የሜድቴሽን ማእከል መምህር ሲሆን ትምህርቶቹ አለም አቀፍ ተመልካቾችን የሚስብ ነው።

Copyright © 2026
Made with ❤️ By Joe