Update Quote

Update Well Said Quotes .

Author Title
Category Quote inamharic
Loading...

Glossary

ሜድቴሽን (Meditation)

ቁጭ ተብሎ ትንፋሽን ልብ ማለት ወይም ረጋ ብሎ በመራመድ አካልና አእምሮን የመገንዘብ ልምምድ

ማስተዋል (Mindfulness)

ነገሮችንን ሁኔታዎችን ረጋ ባለ ቀልብ ማየት

ቡዲሂዝም (Budhhism)

ሳዳርታ ጎታማ የተባለ ህንዳዊ ስለአእምሮአቸን እውነታ ያስተማረው ትምህርት ስም።

ዳሃማ (Dhamma)

ቡዳህ ያስተማረው ትምህርት

አራቱ እውነቶች (4 Noble Truths)

የቡድሃ አስተምህሮ ዋና አካል የሆነ፣ ስቃይና እና እርካታ የማጣት እንዳለ የሚያመለክት ከዛ መንስኤውንና ማቆም እንደምንችልና እንዴት እንደምናቆመው የሚያሳየን ትምህርት ነው።

ፍቅራዊ ደግነት (Loving-Kindness)

ለሁሉም ፍጥረታት ከራስ ጀምሮ ከሥቃይ እና ከስቃይ ምክንያቶቹ ነፃ እንዲሆኑ የመሻት ጥልቅ ፍላጎት እና ምኞት።

ሱታ (Sutta)

በቡድሃ ያስተማረውን ትምህርት የያዘ መመሪያ

የነቃ (Awaken )

አእምሮአዊ ስቃይ በሚቆምበት ግዜ የምንጠቀመው ቃል። ለቡዳ ይህ ቃል የተሰጠው አእምሮአዊ ስቃዩን ማቆም ስለቻለ ነው።

አጃን (Ajahn)

የታይላንድ ቃል፣ ለአስተማሪ ወይም ለአማካሪ።

ቢኩ (Bhikkhu)

የቡድሂስት መነኩሴ

ዘን (Zen)

በቻይንኛ ቻን ተብሎ የሚጠራ ቻይና ውስጥ የዳበረ የቡዲስት የሜድቴሽን አይነት ከአምስተኛው እስከ ሰባተኛው ክፍለ ዘመን ደግሞ ወደ ጃፓን እና ኮሪያ ተሰራጭቶ ዘን ተብሎ የሚጠራ ልምምድ።

ጊዜያዊነት (Impermanent)

ሁሉም ነገር ጊዜያዊና የሚለዋወጥ መሆኑን፣ ከሥጋዊ ነገሮች እስከ ሀሳቦች እና ስሜቶች ድረስ፣ እነዚህን የሚገልጽ የቡዲዝም ትምህርት።

መጣበቅ (Attachment)

የሚያልፉ ሁኔታዎችና ነገሮችን የደስታና የምኞቶች መንስኤ አደርጎ የሚቆጥር የተታለለ የአእምሮ ሁኔታ።

ማራ (Mára )

በቡድሂዝም ውስጥ የሚታወቀው ሰዎችን በመፈታተን ነው፣ ሱታዎች ላይ የተወከለው እንደ ክፉ አስተሳሰብ ያለው ሃይል ሰዎችን ከነጻነት መንገድ ለማራቅ የሚሞክር ሃይል ነው። ተሯሚዎች ማራን የክፉ ኃይሎች ጌታ፣ እንደ አእምሮ ርኩሰት እና እንደ ሞት ያስረዱታል።

ባዶነት፡ (Emptiness )

ነገሮችና ሁኔታዎች ራሳቸውን ችለው እንደማይነሱ፣ ነገር ግን እርስ በርስ የተያያዙ እና ከተፈጥሯዊ ወይም የተለየ የራስ ህልውና ባዶ መሆናቸውን የሚያመለክት ቃል ነው።

Thich Nhat Hanh

— Vietnamese Zen Buddhist Monk Born: October 11, 1926 Died: January 22, 2022

ውጥረት ስለሰውነት

In our body there may be tension and pain. If we suppress or ignore this, then every day the tension and pain will grow and prevent us from experiencing the happiness that we should be able to experience. When we have tension in our body, we can’t sleep well or eat well. Mindfulness of breathing can help us relax and bring peace to our body. We take care of our body first. We can take care of our mind later.

In Amharic

በሰውነታችን ውስጥ ውጥረት እና ህመም ሊኖር ይችላል። ይህንን ካፈንን ወይም ችላ ካልን በየቀኑ ውጥረቱ እና ህመሙ እየጨመረ ይሄዳል እናም ልናገኘው የምንችለውን ደስታ እንዳናጣጥም ያደርገናል። በሰውነታችን ውስጥ ውጥረት በሚፈጠርበት ጊዜ በደንብ መተኛት ወይም በጥሩ ሁኔታ መመገብ አንችልም። እስትንፋሳችንን ልብ ማለት ዘና ለማለት እና ለሰውነታችን ሰላም ለማምጣት ይረዳናል። በመጀመሪያ ሰውነታችንን እንንከባከባለን። ከዛ በኋላ አእምሮአችንን መንከባከብ እንችላለን።

About

የቪዬትናም ቡዲስት መነኩሴ፣ የሰላም ታጋይ፣ የተዋጣለት ደራሲ፣ ገጣሚ እና መምህር ነበር፣ የፕለም መንደር ወግን የመሰረተ፣ በታሪክ ለተሳትፎ ቡዲዝም እንደ ዋና መነሳሳት ይታወቃል። "የአስተሳሰብ አባት" በመባል የሚታወቀው Nhất Hạn በምዕራባውያን የቡድሂዝም ልምምዶች ላይ ትልቅ ተጽዕኖ ነበረው።

Copyright © 2026
Made with ❤️ By Joe