Update Quote

Update Well Said Quotes .

Author Title
Category Quote inamharic
Loading...

Glossary

ሜድቴሽን (Meditation)

ቁጭ ተብሎ ትንፋሽን ልብ ማለት ወይም ረጋ ብሎ በመራመድ አካልና አእምሮን የመገንዘብ ልምምድ

ማስተዋል (Mindfulness)

ነገሮችንን ሁኔታዎችን ረጋ ባለ ቀልብ ማየት

ቡዲሂዝም (Budhhism)

ሳዳርታ ጎታማ የተባለ ህንዳዊ ስለአእምሮአቸን እውነታ ያስተማረው ትምህርት ስም።

ዳሃማ (Dhamma)

ቡዳህ ያስተማረው ትምህርት

አራቱ እውነቶች (4 Noble Truths)

የቡድሃ አስተምህሮ ዋና አካል የሆነ፣ ስቃይና እና እርካታ የማጣት እንዳለ የሚያመለክት ከዛ መንስኤውንና ማቆም እንደምንችልና እንዴት እንደምናቆመው የሚያሳየን ትምህርት ነው።

ፍቅራዊ ደግነት (Loving-Kindness)

ለሁሉም ፍጥረታት ከራስ ጀምሮ ከሥቃይ እና ከስቃይ ምክንያቶቹ ነፃ እንዲሆኑ የመሻት ጥልቅ ፍላጎት እና ምኞት።

ሱታ (Sutta)

በቡድሃ ያስተማረውን ትምህርት የያዘ መመሪያ

የነቃ (Awaken )

አእምሮአዊ ስቃይ በሚቆምበት ግዜ የምንጠቀመው ቃል። ለቡዳ ይህ ቃል የተሰጠው አእምሮአዊ ስቃዩን ማቆም ስለቻለ ነው።

አጃን (Ajahn)

የታይላንድ ቃል፣ ለአስተማሪ ወይም ለአማካሪ።

ቢኩ (Bhikkhu)

የቡድሂስት መነኩሴ

ዘን (Zen)

በቻይንኛ ቻን ተብሎ የሚጠራ ቻይና ውስጥ የዳበረ የቡዲስት የሜድቴሽን አይነት ከአምስተኛው እስከ ሰባተኛው ክፍለ ዘመን ደግሞ ወደ ጃፓን እና ኮሪያ ተሰራጭቶ ዘን ተብሎ የሚጠራ ልምምድ።

ጊዜያዊነት (Impermanent)

ሁሉም ነገር ጊዜያዊና የሚለዋወጥ መሆኑን፣ ከሥጋዊ ነገሮች እስከ ሀሳቦች እና ስሜቶች ድረስ፣ እነዚህን የሚገልጽ የቡዲዝም ትምህርት።

መጣበቅ (Attachment)

የሚያልፉ ሁኔታዎችና ነገሮችን የደስታና የምኞቶች መንስኤ አደርጎ የሚቆጥር የተታለለ የአእምሮ ሁኔታ።

ማራ (Mára )

በቡድሂዝም ውስጥ የሚታወቀው ሰዎችን በመፈታተን ነው፣ ሱታዎች ላይ የተወከለው እንደ ክፉ አስተሳሰብ ያለው ሃይል ሰዎችን ከነጻነት መንገድ ለማራቅ የሚሞክር ሃይል ነው። ተሯሚዎች ማራን የክፉ ኃይሎች ጌታ፣ እንደ አእምሮ ርኩሰት እና እንደ ሞት ያስረዱታል።

ባዶነት፡ (Emptiness )

ነገሮችና ሁኔታዎች ራሳቸውን ችለው እንደማይነሱ፣ ነገር ግን እርስ በርስ የተያያዙ እና ከተፈጥሯዊ ወይም የተለየ የራስ ህልውና ባዶ መሆናቸውን የሚያመለክት ቃል ነው።

Thich Nhat Hanh

— Vietnamese Zen Buddhist Monk Born: October 11, 1926 Died: January 22, 2022

መልቀቅ ስለአእምሮ

To “let go” means to let go of something. That something may be an object of our mind, something we’ve created, like an idea, feeling, desire, or belief. Getting stuck on that idea could bring a lot of unhappiness and anxiety. We’d like to let it go, but how? It’s not enough just to want to let it go; we have to recognize it first as being something real. We have to look deeply into its nature and where it has come from, because ideas are born from feelings, emotions, and past experiences, from things we’ve seen and heard. With the energy of mindfulness and concentration we can look deeply and discover the roots of the idea, feeling, emotion, or desire. Mindfulness and concentration bring about insight, and insight can help us release the object in our mind.

In Amharic

"መልቀቅ" ማለት አንድን ነገር መተው ማለት ነው። በአእምሯችን የፈጠርነውን ነገር እንደ ሀሳብ፣ ስሜት፣ ፍላጎት ወይም እምነት ሊሆን ይችላል። በነዚህ ሀሳብ ላይ መጣበቅ ስጋትና ጭንቀትን ያመጣል። መልቀቅ እንፈልጋለን፣ ግን እንዴት? ለመልቀቅ መፈለግ ብቻ በቂ አይደለም፣ መጀመሪያ እንደ እውነተኛ ነገር ልንገነዘበው ይገባል። ተፈጥሮአቸውንና እና ከየት እንደመጡ በጥልቀት መመርመር ይኖርብናል፣ ምክንያቱም ሀሳቦች ከስሜት እና ካለፉት ልምዶች ፣ ካየናቸው እና ከሰማናቸው ነገሮች የተወለዱ ናቸው።በመስተዋል እና በትኩረት ሃይል በጥልቀት መመልከትና የሃሳቦቹን፣ የስሜቶቹን ወይም የፍላጎቶቹን መነሻ ማወቅ እንችላለን። እነዚህ ትኩረት ሰጥተን ልብ ማለት ማስተዋልን ያመጣል፣ እና ማስተዋላችን በአእምሯችን ያለውን ነገር ለመልቀቅ ይረዳናል።

About

የቪዬትናም ቡዲስት መነኩሴ፣ የሰላም ታጋይ፣ የተዋጣለት ደራሲ፣ ገጣሚ እና መምህር ነበር፣ የፕለም መንደር ወግን የመሰረተ፣ በታሪክ ለተሳትፎ ቡዲዝም እንደ ዋና መነሳሳት ይታወቃል። "የአስተሳሰብ አባት" በመባል የሚታወቀው Nhất Hạn በምዕራባውያን የቡድሂዝም ልምምዶች ላይ ትልቅ ተጽዕኖ ነበረው።

Copyright © 2026
Made with ❤️ By Joe