Thich Nhat Hanh
— Vietnamese Zen Buddhist Monk Born: October 11, 1926 Died: January 22, 2022
ህይወታችሁን አታባክኑ
ስለሜድቴሽን
On the wooden board outside of the meditation hall in many Zen monasteries, there is a four-line inscription. The last line is, “Do not squander your life.” Our lives are made of days and hours, and each hour is precious. Have we wasted our hours and our days? Are we wasting our lives? When we practice sitting or walking meditation, it’s easier to be mindful and concentrated. During the rest of the day, we also practice. It’s more difficult, but it’s possible. The sitting and the walking can be extended to the non-walking, non-sitting moments of our day. That is the basic principle of meditation.
In Amharic
በብዙ የዘን ገዳማት ከሜዲቴሽን አዳራሽ ውጭ ባለው የእንጨት ሰሌዳ ላይ ባለ አራት መስመር ጽሑፍ አለ። የመጨረሻው መስመር “ህይወትህን አታባክን” የሚል ነው። ህይወታችን በቀናት እና በሰአታት የተሰራ ነው፣ እና እያንዳንዱ ሰአት ውድ ነው። ሰአታችንን እና ቀኖቻችንን እያባከንን ነው? ህይወታችንን በአላስፈላጊ ነገር እያወሳሰብነው ነው? የመቀመጥ ወይም የእርምጃ ሚድቴሽን ስንለማመድ ግን ቀላል ይሆንልናል። በሌላው ሰአትም ልምምዳችን ይቀጥላል። ይከብዳል ግን ይቻላል። የመቀመጥና የመራመድ ልምምዳችን ወደማንራመድባቸው እና ወደማንቀመጥባቸው ጊዜያትም ይራዘማል። ይህ የሜድቴሽን መሰረታዊ መርህ ነው።
About
የቪዬትናም ቡዲስት መነኩሴ፣ የሰላም ታጋይ፣ የተዋጣለት ደራሲ፣ ገጣሚ እና መምህር ነበር፣ የፕለም መንደር ወግን የመሰረተ፣ በታሪክ ለተሳትፎ ቡዲዝም እንደ ዋና መነሳሳት ይታወቃል። "የአስተሳሰብ አባት" በመባል የሚታወቀው Nhất Hạn በምዕራባውያን የቡድሂዝም ልምምዶች ላይ ትልቅ ተጽዕኖ ነበረው።